እንዲህ ነን እኛ!!

ወገኖቼ እንዴት ናቸሁ?ክረምቱ እንዴት ይዟቹሃል? ለነገሩ ዛሬ ላወጋቹህ የፈለኩት ስለክረምትም አይደለ፡፡ ስለ እኛ-ስለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እንጂ፡፡ እንደምናዉቀዉ ሀገራችን በለፉት ሀያ አመታት በከፍተኛ ትምህርት መስክ አመርቂ ዉጤት አስመዝግባለች፡፡ ይህ ሀቅ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ድረስ የከፍተኛ ትምህርት ችግሮች ብዙ ናቸዉ፡፡ ለምሳሌ የትምህረት ጥራት ችግር፡፡ በመላዉ ሀገሪቱ በአሁን ሰዓት ከ33 በላይ የመንግሰት ዩኒቨርሲቲዎች ይገኛሉ፡፡በርከት ያሉ የግል ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆችም አሉ፡፡ እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎችንና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ መምህራንን የያዙ ናቸዉ፡፡

እኛ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ተማሪዎችን በመቅረፅና ለስኬት ለማብቃት ያለን ድርሻ በጣም ትለቅ ነዉ፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለዉ እኛ ከኛ የሚጠበቀዉን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት ስንችል ነዉ፡፡ አንዳነድ ግዜ ስለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ሳስብ የሚገርሙኝ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ የዩኒቨርሲተ ተማሪ ከነበርኩበት ግዜ ጀምሮ አሁን መምህር ሆኜ እያገለገልኩ እስካለሁበት ግዜ ድረስ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ስታዘብ ቆይቻለሁ፡፡ እራሴንም ጭምር ማለቴ ነዉ፡፡ እኛ የዩኒቨርሲቲ መምህራን የምንወደስበትና የምንወቀስበት ብዙ ነገሮች አሉን፡፡

በዚህም መሰረት ብዙዎቻችን ስራችንን የምናከብር፤ በሰዓት ክፍል የምንገባ፤ ህግን የምናከብር፤ ተማሪን የምናከብር ፤ ራሳችንን የምናከብር ፤ አንድ መምህር ሊኖረዉ የሚገባዉን ብቃት/ኳሊቲ ያለን፤ ለምሳሌ ሁሌ የምናነብ፤ ሁሌ የምንዘጋጅ፤ ተማሪዎቻችንን ምን ማስተማር እነዳለብን የምናዉቅ፤ የማስተማሪያ ቋንቋን (እነግሊዘኛን ማለቴ ነዉ) በደንብ አድርገን የምንጠቀም፤ ተማሪዎቻችንን የምናበረታታ፤ motivate and inspire የምናደርግ፤ ለተማሪዎቻችን ምሳሌ የሆንን፤ ፈተና በወጣዉ የግዜ ሰሌዳ መሰረት የሚንፈትን፤ ዉጤት ለተማሪዎቻችን በግዜ የምናሳይና feedback የምንሰጥ ነን፡፡

እነዲሁም ብዙዎቻችን ለተማሪዎች ግሬድ በዉጤታቸዉ መሰረት ብቻ የምንሰጥ፤ ደካማ ተማሪዎችን ከመሳደብ ይልቅ በመቅረብ ችግሮቻቸዉን ለመረዳት የምንሞክርና እገዛ የምናደርግ፤ታታሪና ትጉህ የሆን፡ ሀገረን የሚጠቅም ብዙ ምርምሮችን የምንሰራ፤ ለስራችን ከሀገር ዉስጥና ከሀገር ዉጭ እዉቅና ያገኘን የተሸለምን፤አንቱታን ያተረፍን፤ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወደ ሀገር ያስገባን፤ ወጣት መምህራንና ተመራማሪዎችን የምናበረታታ የምንደግፍ ልመዳችንን የምናካፍል፤ከገንዘብና ዝና ይልቅ ለህዝባችንና ሀገራችን ሌት ከቀን የምንሰራ፤ ፕሮፌሰር ነኝ ወይም ዶክተር ነኝ በማለት የማንኳፈስ የማንጠባረር ነን፡፡

በተቃራኒዉ አንዳንዶቻችን የማስተማር ብቃት የለለን (በነገራችን ላይ ማስተማር አልችልም የሚል የለም፤ ሁሉም ሰዉ ራሱን እነደ ጎበዝ አስተማሪ ነዉ የሚያያዉ)፤ የማናነብ፡የማንዘጋጅ ፤በእነግለዘኛም ሆነ በአማርኛ መስተማር የማንችል፤ መጠጥ ጠጥተንና ሰክረን ክፍል የምንገባ፤ ተማሪ ቀጥረን የምንቀር፤ በሰዓት ክፍል የማንገባ፤በአግባቡ የማናስተምር፤ ስለምናስተምረዉ ነገር ምንም የማናዉቅ፤ በክፍል ዉሰጥ ስለራሳችን ብቻ በማዉራት ግዜ የምናባክን፤ ተማሪዎችን ከመሬት ተነስተን የምንሳደብ፤ተማሪዎችን ምንም ሳያጠፉ ከክፍል የምናባርር፤ ፤ፈተና ፈትነን ዉጤት የማናሳይ feedback የማንሰጥና ፈተና ሳንፈትን ዉጤት ለተማሪዎች የምንሰጥ ነን፡፡

አንዳንዶቻችን course outline ብቻ ሰጥተን ሳናስተምር ፈተና የምንፈትን፤ ተማሪዎቻችንን በስራቸዉ ሳይሆን ብሄርን ሀይማኖትን ፆታን ትዉዉቅን መሰረት በማድረግ ግሬድ የምንደለድል፤የተማሪዎቻችንን ችግሮች ለማድመጥ ፍቃደኛ ያልሆንን ፤ ተማሪዎችን ከማበረታት ይልቅ ሞራላቸዉን የሚነካ ስድብ የምንሳደብ፤ከተማሪዎቻቸን ጋር ለመደባደብ ራሳችንን የምንጋብዝ፤ የPHD ትምህርታችንን በጀመርን ማግስት “ዶክተር ኤከሌ ነኝ” እያለን ለተማሪዎቻችን ራሳችንን የምናስተዋዉቅ፤ዝም ብለን በባዶ ሜዳ የምንጎርር፤ ዉጭ ሀገር ተምረን ተመልሰን ከሆነ ስለተማርንበት ሀገር ምክንያት እየፈለግን በየደቂቃዉ እያነሳን የምንተርክ፤ ተማሪዎችን “እያንዳነድሽ ‘F’ ሰጥሻለሁ” ብለን የምናስፈራራ ነን፡፡

አንዳንዶቻችን ሴት ተማሪዎችን እነደዘህ ወይም እነደዛ ካላደረክሽ ዉጤትሽን አበላሻለሁ የምንል፤ተማሪዎች ጥያቄ ሲጠይቁን ዐይናችን ላይ የደረግነዉን መነፅር ዝቅ በማድረግ በግልምጫ የምናነሳ፤ የ2ሰአት ክላስን በ20 ደቂቃ የምንጨርስ፤ አራት ወይም አምስት ቻፕተሮችን በአንድ ሰዓት ሌክቸር የምናገባድድ ፤ handout ለተማሪዎች ሰጥተን ክፍል የማንገባ፤ ብዙ F መስጠት(ተማሪዉ ዉጤት እያለዉም ጭምር) የሚያሰደስተን የሚያዝናናን ፤ ያላስተማርነዉን በመፈተን የሱ ወይም የሷ ፈተና በጣም ከባድ ነዉ እንድባልልን የምንፈለግ፤ የምርጫ ፈተና ስንፈትን እስከ “H” ድረስ የምናወጣ፤ የሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ደሞዝ እየተከፈለን የምናስተምር (በሁለት ዩኒቨርሲቲዎች full time አስተማሪ በመሆን ማለቴ ነዉ-በምን አይነት ህግ እነደዛ እነደሚቻል ባላዉቀም)፤ የስራባልደረቦቻችንን የሚንንቅ የሚንዘልፍ፤ተማሪዎች ዘነድ ተወዳጅ ለመሆን ገሬድ በነፃ የምንሰጥ ነን፡፡

አንዳንዶቻችን የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ሆነን በአማርኛ የምናስተመር ነገር ግን ያለኛ በስተቀር ሌሎች እነግሊዘኛ ማስተማር አይችሉም ብለን የምናስብ፤ ያለ power point መናገርም ሆነ ማስተማር የማንችል ፤ፈተናና አሳይመንት ሳናርም ዉጤት ለተማሪዎች የምንሰጥ (ሁለተኛ አመት ተማሪ በነበርኩበት ግዜ አንድ አስተማሪየችን ፈተናችንን ሳያርም ገሬድ ሰጥቶናል፤ሀላችንም አሪፍ ግሬድ ነዉ የዛቅ ነዉ)፤ ዉጭ ላይ business በማጧጧፍ የዩኒቨርሲቲ ስራን ሙሉ በሙሉ የምንዘነጋ፤ የተማሪን ወጤት ሳናስገባ የምንጠፋና ተማሪዎቸን የምናከራትት፤እራሳችን ብንጠየቅ መመለስ የማንችለዉን ጥያቄ ከእነተርኔት ገለብጠን የምንፈትን፤ ምሽት ላይ ከተማሪዎቻችን ጋራ get down የምንል፤ተማሪዎቻችን እነደ መምህር ሳይሆን እንደ አምለክ እነዲያዩን የምንፈለግ ነን፡፡

አንዳንዶቻችን ሀላፊ ለመሆን አቋሯጭ መንገዶችን ሁሉ የምንጠቀም (ስራ ለመስራት ሳይሆን ትንንሽዬ ሳንቲሞችን ለመሰብሰብ)፤ ምንም ፋይዳ የለላቸዉንና ለዉጥ የማያመጡ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችን በማዘጋጀት የዩኒቨርሲቲ ገንዘብ ወደ ኪሳችን እንዲገባ ሌተ ተቀን የምንሰራ፤ ሀላፊ ሆነን ስንሰራ ለመምህራን የተለያዩ ዕድሎች (opportunities) ሲመጡ የምንደብቅ ወይም deadline ካለፈ በኋላ መስታወቂያ የምንለጥፍ ወይም ደግሞ ለቀርብ ጓደኞቻችን ብቻ ተጠቃሚ እነድሆኑ የምናደርግ፤ካፌ ሂደን ማክያቶ እየጠጣን ለሁለትና ሶስት ሰዓታት ሰዉን ስናማ ዉለን ወደ ቤታችን የምንገባ፡ በትምህርት ሰዓት ወንበር ስበን በመቀመጥ የልጅነት ታሪካችንን የምናወራ፤በሰሌዳ ላይ ከጫፍ ጫፍ ፅፈን ስላነበብን ብቻ ጥሩ አድርገን ያስተማርን የሚመስለንና ተማሪዎቸን ያለምክናያት የምናገላታ የምናሰቃይ ነን፡፡

አንዳንዶቻችን ተማሪዎቻችን ለበላይ አካል ሲከሱን ዉጤታቸዉን በማበላሸት የምንበቀል፤ የዶክትሬት ድግሪያችንን ወስደን በመጣን መግሰት በፈተና ወረቀት ላይ በ headerና በ footer መልክ ዶክተር ኤከሌ በማለት በየአነዳንዱ ገፅ ላይ የምንፅፍ፤ የPHD holder ሆንን ሰዎች በስህተት አቶ ኤከሌ ብለዉ ቢጠሩን እንኳ “አንተ/አንቺ እኔ እኮ ዶክተር ነኝ እነዴት አቶ ትለኛለህ” ብለን ሰዎችን በቁጣ የምናስደነግጥ፤ተዝቆ የማያልቅ ዕዉቀት እያለን ማስረዳት የማንችል፤እራሳችን ገራ ተጋብተን ተማሪዎችን ገራ የምናጋባ ነን፡፡ አረ ባካችሁ ተዉኝ…… የኛ ጉድ እኮ ተወርቶ ተፅፎ የሚያልቅ ነገር አይደለም፡፡ ይህንን ፅሑፍ የምታነቡ ሰዎች (አብዛኞቻቹህ በዩኒቭርሲቲ ህይወት ዉሰጥ ያለፋቹ ስለሆናቹህ) የተቀረዉን የዩነቨረሲቲ መምህራንን ጥንካሬዎችና ድክመቶችን በማስመልከት የየራሳቹን አስተያያት መስጠት ትችላላቹህ)፡፡ ብዙዎቻችን ከጥንካሬያችን ይልቅ ድክመታችን ይበዛል፡፡ እዉነቱን ለመናገር እነደዚህ ያሉ ደካማ አሰራሮችንና አስተሳሰቦችን ካላስቀረን በቀር የምናስተምራቸዉ ተማሪዎች በትምህርታቸዉ ዉጤታማ፤ ለሀገር ለወገን የሚያስቡና የሚሰሩ መሆናቸዉ አጠራጣሪ ነዉ፡፡ ምክኒያቱም ለተማሪዎቻችን ጥሩ ምሳሌ መሆን አልቻልንማ!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s