የናፍቁኝ የሀገር ቤት ነገሮች

ወዳጆች እንዴት ናቹህ? ሰላም ናቹህ አይደል? እንኳን ሰላም ሆናቹልኝ፡፡ በጣም እኮ ነዉ የናፈቃቹኝ፡፡ ያዉ እንግድህ እነደምታዉቁት በተለያየ ምክንያቶች ሰዉ ከሀገር ከወጣ በኋላ ብዙ የሀገር ቤት ነገሮች ይናፍቁታል፡፡ እኔም ኖርዌይ የሚትባል ሀገርም አይደል ያለሁት፡ለትንሽዬ ግዜም ብትሆን፡፡ የናፍቁኝ በጣም ብዙ የሀገር ቤት ነገሮች አሉ፡፡ ከምንም በለይ ቤተሰቤ፤ ዘመዶቼና ጓደኞቸቼ ናፍቆዉኛል፡፡፡አሁን ባለሁበት ሁኔታ ግን በጣም በጣም የናፋቁኝ ነገሮች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

የመብራት በየሰአቱ መቆራረጥ፤
የዉሃ በሳምንት ወይም በሁለት ሳምንት አንዴ መምጣት፤
የኔትወረክ በየደቂቃዉ መቆራረጥ፤
የመኪና አሽከርካሪዎች እናትህን እንዲ ላርጋት ስድብ፤
በየሰፈሩ ሙንታረቦ የሚያስጨሁ ሙዚቃ ቤቶችና ሻይ ቤቶች፤
ከቤተ እመነቶች የሚወጡ አዋኪ ድምፆች፤
ያለገደብ የሚጮህ የመኪና ክላክስ፤
ለሱካርና ለዘይት ለቀናት መስለፍ፤
ታክሲ ለመጠበቅ የሚደረግ በጣም ረዣዥም ስልፎች፤
የወንዶች ሴት ልጆችን መዛለፍ፤
ከተማ ዉሰጥ በየቦታዉ የተቆፈሩ ጉርጓዶችንና በየቦታዉ የሚፈሱ የሽንትቤት ቆሻሻዎች፤
በየመንገዱ ዳር የሚሸና ሰዉ፤
የትራፊክ መብራት ሲበራ ሰዎች በሚያቋርጡበት መንገድ ላይ መኪናን ማቆም፤
ቆመጥና ዱላ ይዘዉ ሰዉ ላይ የሚያፈጡና የሚያስፈሩ የህግ አስከባሪዎች፤
በጣም ዝናባማና ብርዳማ በሆነ ወቅት ላይ በጣም ትንሺዬ ቁምጣና በጣም ስስ የሆነችቶፕ ለብሰዉ የሚወጡ ሴቶች፤

ሌሎች የናፈቁኝ ነገሮች በጣም ብዙ አሉ፡፡እነሱን ሌላ ጊዜ ነግራቹሀለዉ፡፡ ለአሁን ግን እዚ ላይ ይብቃኝ፡፡ ቻዎቻዎ!!!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s