የጋዜጠኛነት ስራ ራስን ግራ አጋብቶ ሌላዉን ግራ ማጋባት አይደለም

ወዳጆቼ እነዴት ናቹሁ?ፕረዘዳንት ኦባማ ሀገራችንን ከጎበኙ በኃላ ህይወት እንዴት ይዟቿል? የኔ በሚገርም ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ የናንተስ? ”የአንተ እንዴት ሆኖ?” እንዳትሉኝ ብቻ፡፡ እነዲሁ ስቀልዳቹ ነዉ፡፡

በተለያዩ ግዜያት ለሰሩት መልካም ስራና ላበረከቱት አስታውፅዖ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የክብር ዶክትሬት ያገኙትን ግለሰቦች ”የክብር ዶክተር አርቲሰት ኤከሌ፤ የክብር ዶክተር ጀግናዉ ሻለቃ አትሌት ኤከሌ፤ የክብር ዶክተር ደራሲ ኤከሌ ብለዉ መጥራት የሚወዱ ጋዜጠኞቻችን ምነዉ ፕረዘዳንት ኦባማ ሀገራችንን ሲጎበኙ በነበሩበት ወቅት የክብር ዶከተር ፕረዘዳንት ባራክ ኦባማ ብለዉ ያልጠሯቸዉ? እሳቸዉም የክብር ዶክትሬት ከሙርሀዉስ ኮሌጅ በ2013 አግኝተዋል እኮ፡፡ ወይስ ፕረዘዳንቱ የክብር ዶክትሬት እነደተሰጣቸዉ ሳይሰሙ ኑረዋል?

እነዴት ነዉ ነገሩ? የክብር ዶክተር የሚለዉ መጠሪያ የሚሰራዉ የክብር ዶክትሬት ላገኙ የኢትዮጵዊያን አትሌቶች፡ አርትስቶችና ደራሲዎች ብቻ ነዉ እነዴ?ስጀመር የክብር ዶክተር የሚባል የመጠሪያ ማዕረግ (Title) የለም፡እኔ እሰከማዉቀዉ ድረስ፡፡ግን ይህን የመጠሪያ ማዕረግ ብንጠቀምበት ምንም ችገር የለዉም ብለን የምናስብ ከሆነና ከተስማማንበት ደግሞ በአግባቡና ወጥነት ባለዉ መልኩ መጠቀም ግድ ይላል የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡የጋዜጠኛነት ስራ ራስን ግራ አጋብቶ ሌላዉን ግራ ማጋባት አይደለም!

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s