ዘረኛ ማነዉ?

በኢትዮጲያችን ዘረኛና ዘረኝነት የሚባሉ ቃላት በተደጋጋሚ ሁኔታ ሲነሱ መስማት የተለመደ ነገር እየሆነ መጥቷል፡፡ በሶሻል ሚዲያ ላይም ሰለነዚህ ጉዳዮች መፃፍም መከራከርም ከግዜ ወደ ግዜ እየተጧጧፈ ይገኛል፤ይህንን ማድረግ ለብዙዎቻችን እንደ ሆቢም እየሆነ ነዉ፡፡ እኔም (እንደ ሌሎች ሁሉ)የሶሻል ሚዲያዉ የሰጠኝን የመፃፍና የመናገር መብት በመጠቀም ስለዚህ ጉዳይ የራሴን ሀሳብ ልስጥበት ወይ ብዬ አሰብኩ፡፡ የእኛን ሀገር ሁኔታ ከግምት ወስጥ በማስገባት ዘረኛ ግን ማነዉ? ብዬ ራሴን ጠየኩ፤ ምክኒያቱም አንዱ ግለሰብ/ቡድን/ብሔር ልለኛዉን ግለሰብ/ቡድን/ብሔር ዘረኛ ሲል እንሰማለን፤እናነባለን፡፡ለዚህም ጥያቄ መልሱ እንደሚከተለዉ ተከሰተልኝ፡፡

እንግዲህ እኔ እሰከሚገባኝ ድረስ አንድ ሰዉ፡ ቡድን ወይም ብሔር ሊሆን ይችላል፤ ዘረኛ የሚባለዉ የኔ ወይም የኛ ዘር ወይም ብሔር ከሌላዉ ብሔር ወይም ዘር በመልክ፡በአስተሳሰብ፤ በቋንቋ፡ በባሕል፡በእምነት፤ከሌላዉ ብሔር የተሸለ ወይም የሚበልጥ ነዉ ብሎ የሚያስብና ያንን ተግባራዊ ሲያደረግ ወይም ተግባራዊ ለማድራግ ሲሞክር ነዉ፡፡ዘረኛ የሆነ ሰዉ ወይም ቡድን የልላዉን ግለሰብ መልክ ወይም ቀለም፤ የልለዉን አስተሳሰብ፡ የሌላዉን፡ቋንቋ፤ የልላዉን ባሕልና እምነትይጠላል፤ያንቋሽሻል፡፡ያለ ራሱ ማንነት በቀር የሌላዉ ማንነት በምንም አይነት ሁኔታ ቦታ እነዳይኖረዉ ቀን ከሌት ይሰራል፤ ያለ የሌለ ሀይሉን በመጠቀምም ሌላዉን ለማጥፋት ደፋ ቀና ይላል፡፡

የሱን የበላይነት የማይቀበለዉን ግለሰብ ወይም ብድን በጠላትነት ይፈርጃል፡፡ለዚህ ሰዉ/ቡድን/ብሔር እኔ ካንተ ጋር እኩል ነኝ እንጂ የአንተ የበታች አይደለዉም ብሎ ማለት በጣም ያብገነዋል፡፡ሌሎች እኛ ካንት አኩል ነን፡ ላንተ የሚገባዉ ሁሉ ለኔም ይገባኛል፤ እኩልነትና ፍትህ መኖር አለበት፤ አንተ ስተበላ እኛ መራብ የለብንም፡ አንተ የራስህን ቋንቋ፤በሕልና እምነት ስታሳድግ ስታለማ እኔም እነደዛዉ ማድራግ አለብኝ፤ ይህንን የማድረግ መብትና ነፃነት ተፈጥሯዊ ስለሆነ ልትነፈገኝ አይገባም ማለት ለዛ ዘረኛ ለሆነ ሰዉ/ቡድን/ብሔር ይህ ጥያቄ በምንም አይነት ሁኔታ ተቀባይነት የለዉም፡፡

የኔን ማንነት አጥፍተህ የራስህን በኔ ላይ መጫን አትችልም ማለት ክፋትም ሀጥያትም ነዉ፡፡ ለዘህ ሰዉ/ቡድን/ብሔር ተከባብረን አብረን እንኑር ማለት ሞት ነዉ፡፡ ይህ ሰዉ/ቡድን/ብሔር አንተ የበላይ አይደለህም፡ከኛ ጋር እኩል ነህ እንጂ ሲባል አሸፈረኝ ይላል፡፡ ዘረኛ የሆነ ሰዉ ሁሌ ልለኛዉን ሰዉ መጨፍለቅ ይፈልጋል፤ማጥፋትንም ጭምር፡፡በተለያዩ ሀገራት ይታዩ የነበሩ አሁንም እታዩ ያሉ የዘረኝነት ሁኔታዎች በዚህ መንፈስ የተቃኙ ናቸዉ፡፡ ታሪክ የሚነገረን ይሄንኑ ነዉ፡፡ በደቡብ አፍሪካ የነበረዉ የአፓርታይድ ስረዓት፡ በአሜሪካን ሀገር በጥቁሮች ላይ በነጮች ይደርስባቸዉ የነበረዉ በደል፤በሂትለር ዘመን የጀርመኖች በምድር ለይ የእኛ ዘር ከሁሉም ይበልጣል አስተሳስብ፡ በሩወንዳም ቢሆን በ1994 (በፈረንጆች አቆጣጠር)ተፈጥሮ የነበረዉን እጅግ በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ይህንን እዉነታ የሚያሳይ ነዉ፡፡

በኢትዮጲያ ዉስጥም ቢሆን ይህ የዘረኝነት መንፈስ በተለያየ ግዜ ስንፀባረቅ ይታያል፡፡ አንዱ አንድኛዉን ዘረኛ ብሎ ከማለት ዉጭ በትክክል ዘረኛ የሆነዉ ማን እነደሆነ ለመረዳት ግን የቻልን አይመስለኝም፡፡ እስቲ በቅንነት እነመልከት ማነዉ ዘረኛ? የኔ ብሔር ብቻ በሁሉም ነገር የበላይ መሆን አለበት፤ የኔ ቋንቋ ፤የኔ ሀይማኖት ፡ የኔ ባሕል ከሌሎች ይበልጣል፤ ስለዚህ ይህንን መቀበል ግድ የላቹዋል፤ ያ ካልሆነ ኢትዮጲያ የምትባል ሀገር ትጠፋለች ብለዉ ቡራ ከረዩ የሚሉት ናቸዉ ወይስ ሰበኣዊ መብታችን ይከበር፤ የኛም ቋንቋ፡ማንነት፤ ባሕል፡እምነት እነደሌሎቹ ሁሉ መከበር አለባቸዉ ፤እኛም እንደሌሎች ሁሉ በሀገሪቷ የፖለቲካ፤የኢኮኖሚና ማህበራዊ ክንዋኔዎች ፍታዊ በሆነ መልኩ መሳተፍ አለብን፤እኛ እየተናቅን፤እተሰደብን፤እየተንቋሸሽን ፤ከሁለም ነገር ተገለን ተጠቃሚ ሳንሆን መቅረት የለብንም፤ ይህ እሰካልሆነ ድረስ አብሮ መኖርም ሆነ አንድ የሆነችና የበለፀገች ኢትዮጲያን መገነባት አይቻልም ፤ ይህ አስተሳሰብ እሰኪቀየር ድረሰ መታገል አለብን የሚሉት?

እንደኔ እንደኔ ዘረኛ /ብሔረተኛ ከምንባባል ለሁላችንም የምትሆን ኢትዮጲያን ለመፍጠር በአንድለይ መስራት፤ ከዚህ በፊት የነበሩ አስተሳሰቦችን በማስቀረት ሁሉም ሰዎች/ቡድኖች/ሕዝቦች በእኩልነት ተከባብረዉና ተዋደዉ የሚኖሩባትና ሀገር ለመፍጠር መስራት ከያንዳነዳችን ይጠበቃል ብዬ አስባለሁ፡፡ እሰቲ እራሳችንን እንጠይቅ፡፡ ወስጣችንንም እንመርምር፡፡ ዘረኛ ነን ወይስ አይደለንም? ካልሆንን እሰየዉ፤ከሆንን ግን ይህን የአስተሳሰብ ነቀርሳ ከዉስጣችን አዉጥተን በመጣልና የአስተሳሰባችንን ቅኝት በማስተካከል አንዱ የበላይ ሌለኛዉ ደግሞ የበታች ይሁን ሳንል ሁላችንም ተጠቃሚ የሚንሆንባትን ኢትዮጲያ መፍጠር ለነገ የማንለዉ የቤት ስራችን ይመስለኛል፡፡ እኔ እንደዚህ አልኩኝ፤እናንተስ ምን ትላላቹ?

Advertisements

One thought on “ዘረኛ ማነዉ?

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s