ወይ ዲቪ መስጠት!

ሰላም፤ እንዴት ናቹ ወዳጆቼ? እንኳን ለሰንደቅ አላማ ቀን በሰላም አደረሳቹ!እንደዉ እዉነቱን ለመናገር የሰንደቅ አላማን ቀን የምናከብረዉ በፕሮፖጋንዳ፤ በአዋጅ፤በሚዲያ ዘመቻ በአመት አንዴ በአደባባይ በመዉጣት ሳይሆን እኛ ዜጎች የሰንደቅ አላማ ፋይዳ፤ትረጉም ፤መልዕክትና ስሜት ገብቶን በየቀኑ ለሰንደቅ አላማ ያላንን ክብር የምንገልፅበት መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡

ታዲያ ዛሬ የሰንደቅ አላማ ቀን ሲከበር አንዲት ሴትዮ ትክክለኛና እዉነተኛ መረጃዎችን በማቅረብ እንኳን በአፍሪካ በአለም ተወዳዳሪ የማይገኝለት EBC (ወቸዉ ጉዴ፤ BBC መስሎኝ እኮ ነዉ እነደዛ ያልኩት) ላይ ቃለ መጠየቅ ሲደረግላት የተናገረችዉ ነገር ትኩረቴን ስቦት ነበር፡፡ “አሁን የኛ ተራ ነዉ፤ እኛ አንሰደደም፡፡ከአሁን በኋላ እንረሱ (ፈረንጆቹን ማለቷ ነዉ) ናቸዉ ወደኛ በዲቪ መምጣት ያለባቸዉ” ስትል በስሜት(ማለት በኢህድጋዊ ስሜት) ነበር የተናገረችዉ፡፡

እኔ ግን እቺ ግራ የገባትን ሴትዮ ለፈረንጆች ዲቪ መስጠት የሚባለዉን ቅዠት ወደ ጎን እንተዉና፤ በመጀመሪያ በረሀብ እያለቁ ያሉትን ዜጎቻችንን እንመግብ፡፡ በመቀጠል ወደ መካከለኛዉ ምስራቅ ስራ ፍለጋ ሄደዉ በአሰሪዎቻቸዉ በደል የሚደርስባቸዉን እህቶቻችንን ስራ እንፍጠርላቸዉ፡፡በየአመቱ በዲቪ ወደ አሜሪካን የሚሄዱትን በሺ የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን በሰዉ ሀገር ሳይሆን በራሳቸዉ ሀገር ሰርተዉ ሕዝባቸዉን እንዲረዱና ሀገራቸዉን እነዲያለሙ እናድረግ፡፡ ወደ ደቡብ አፈሪካ ለመሄድ ብለዉ በጉዞ ላይ የአንበሳና የነብር ሲሳይ የሚሆኑትን እነዲሁም አዉሮፓ ለመግባት በሰሀራና በሜድትራኒያን ባህር ዉሰጥ የሚያልቁትን ዜጎቻቸችንን በሀገራቸዉ ሰርተዉ እንድኖሩ የተሻለ ዕድል ለመፍጠር መስራት ከምንም በላይ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆን አለበት እላታለሁ፡፡ ለዜጎቿ ያልሆነች ሀገር በታአምር ለሌላ ዜጋ ልትሆን አትችልም፡ ያዉም ለፈረንጆች፡፡ ሰዎች፤ ዲቪ መስጠት አድገናል ተመንድገናል እያሉ የምግብ አርዳታ እንደመጠየቅ ቀላል አይደለም እኮ፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s