እባካቹ መሪዎቻችን ሆይ ለራሳቹ ስትሉ ቆም ብላቹ አስቡ!

በፈጠራቹ ፤ በጉልበታቹ አምላክ፤ እሺ በታላቁ መሪያቹ አጥንት፤ ህዝቡ አልፈልግም ያለዉን ነገር  በጥይት ለማስፈፀም አትሞክሩ! እስክሪፕቶና ደብተር ብቻ ይዘዉ ለተቃዉሞ የወጣዉን ተማሪ አትግደሉ፡፡ የፖለቲካ ስልጣን ዘላለማዊ

አይደለም፡፡ እናንተም የምትዳኙበት ቀን ይመጣል፡፡ አሁን እያደረጋቹ ያላቹት  ተግባር የዘመናቹ መጨረሻ እየመጣ መሆኑን የሚያሳይ ነዉ፡፡ አንድ ሰዉ በገደላቹ ቁጥር ከህዝቡ ጋር ያላቹን ጠላትነት እየጨመራቹ ነዉ ማለት ነዉ፡፡ እስቲ ለራሳቹ ስትሉ ቆም ብላቹ አስቡ፡፡

ታሪክ እነደሚነግረን ጠመንጃ ወደ ሕዝቦቻቸዉ ያዞሩ መንግስታት በምንም አይነት ሁኔታ በስልጣን ላይ መቆየት አልቻሉም፡፡ በመንግሰት ሕዝቡ ላይ የሚደረስ በደልና ጨቆና ሕዝቡ ለነፃነቱና ለመብቱ እንድነሳ ያደርጎዋል፡፡ ያን ግዜ ባለዉ የጦር ሀይል የሚመካዉ መንግሰት መግቢያ ያጣል፡፡ ሕዝቡ አንድ ላይ ከተነሳ ምንም አይነት ሀይል አያቆመዉም፡፡ እንደሱ ቢሆንማ እነ ሳዳም ሁሴን፡ እነ ጋዳፊ፡እነ ሙባረክ፤ ሕዝቡ አንድ ሁኖ የተነሳ ግዜ ያ ለዘመናት የገነቡት የወታደር ሀይል ከሞትና ከእስራት አላተረፋቸዉም፡፡ ለነሱ ታማኝ ሆኖ ይኖር የነበረዉ ወታደር የሕዝቡን የቁጣ መዐበል መቋቋም አልቻለም፡፡ ከሕዝቡ ጋርም ተሰለፈ፡፡

ስለዚህ በወታደር ሀይል መመካት ለግዜዉ ነዉ፡፡ ሕዝቡ እሰኪ ነቃ ድረስ ስልጣን በእጃችን ላይ ለዘላለም የሚቆይ ስለሚመስለን ያሻነዉን ከማድረግ ወደኻል አንልም፡ ዜጎችን እነገድላለን፡ እናሰቃያለን፡እናስራለን፡እናሳድዳለን፡፡ ሕዝቡ አንድ ሆኖ ለመብቱ መፋለም ሲጀምር አሁን  በዜጎች ላይ ለምትፅሙት ግፍና በደል ዉድ ዋጋ መክፈላቹ አይቀርም፡፡ እስከዛዉ ግን ይመቻቹ፡፡እስቲ በእንግሊዘኛ በጣም አጭር  በሆነች ግጥም ብጤ ልምከራቹ፡፡

The more you kill

The more you torture

The more you jail

The more people rise

And bring your power to demise!

#Oromoprotests #Oromo #Ethiopia

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s