የአዲስ አበባ ነገር “ሲስሟት ‘እምቢ’ ብላ ሲስቧት” ሆኗል!

Ethiopian Think Thank Group

ባለፈው ዓመት “ኦሮሚያን ለአመፅ፣ አዲስ አበባን ለቆሻሻ የዳረገች አንቀፅ” በሚል ርዕስ አንድ ፅሁፍ  አውጥቼ ነበር። በፅኁፉ የሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 49(5) ተግባራዊ አለመደረጉ ለተጠቀሱት ችግሮች ምክንያት መሆኑን ይዘረዝራል። በዚህ አመት በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 49(5) መሰረት የኦሮሚያ ክልልን ልዩ-ጥቅም ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ተከትሎ የውዝግቡ ጡዘት ከርሯል። ከሰሞኑ በኦሮሞ ልሂቃን ዘንድ እየተነሳ ያለው ጥያቄ “አዲስ አበባ የኦሮሚያ አካል ናት” የሚል ነው። “ይህ ጥያቄ ከሕገ-መንግስቱ አንፃር እንዴት ይታያል” የሚለውን የዘርፉ ምሁራን ትንታኔ ሊሰጡበት ይችላሉ። ይህ ፅሁፍ ግን ጥየቄውን ከመሰረታዊ የመብት መርህ አንፃር ያለውን አንድምታ ይዳስሳል።

ከሦስት አመታት በፊት በኦሮሚያ ክልል አመፅና ተቃውሞ ሲነሳ “የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ይቁም” በሚል እንደነበር ይታወሳል። በዚህ መልኩ የተጀመረው የፖለቲካ ንቅናቄ ዛሬ ላይ “አዲስ አበባ የኦሮሚያ አካል ናት” ወደሚለው ተቀይሯል። ይህ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ለማወቅ በቅድሚያ ከአመፅና ተቃውሞ በስተጀርባ ያለውን መሰረታዊ ምክንያት መረዳት ያስፈልጋል።

በመሰረቱ፣ አዲስ አበባ ከአመሰራረቷ ጀምሮ በዙሪያዋ ካለው የኦሮሞ ማህብረሰብ ጋር ያላት ግንኙነት ኢ-ፍትሃዊ ነበር። ለብዙ አመታት ከተማዋ በዙሪያዋ ያለውን የኦሮሞ አርሶ-አደር ወደጎን እየገፋችና ከመሬቱ እያፈናቀለች…

View original post 708 more words

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s